A Certificate of Appreciation was presented to the HRF by the South Omo Zone Health Department in recognition of its outstanding contribution over the 2015 fiscal year in facilitating initiatives that reduce maternal, neonatal, and child mortality by enhancing the capacity of healthcare workers and assisting with the purchase of basic medical supplies

ፋውንዴሽኑ በደቡብ ኦሞ ዞን አርብቶ አደር ወረዳዎች በጤናው ዘርፍ ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና ተሰጠው፤

*******************************************************

የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ የኃይለማርያም እና ሮማን ፋውንዴሽን የእናቶች፣የጨቅላ ሕጻናት እና ሕጻናት ሞት ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ በ2015 በጀት ዓመት የጤና ባለሙያዎችን አቅም በማጎልበት እንዲሁም መሰረታዊ የሆኑ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረግ ላበረከተው የላቀ አስተዋጽኦ የምስጋና የምስክር ወረቀት አበረከተ።